ፓስፖርት አገልግሎት
If you are not able to read this page, please download Ge’ez Font click here.
በወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት ወይም ከዚህ ቀደሞ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ፓስፖርት ያልወሰዱና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት 4 ፎቶግራፍ (በከለር የተነሱት ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት፣ ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2. ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ
» ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት ኮፒ
» የወላጆች ዜግነት ማስረጃ (የፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ) ኮፒ
» በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ
» በተቀባይ አገር የተወለዱ ልጆች በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ
» የቀበሌ ወይም የተማሪ መታወቂያ
3. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (የአሻራ መውሰጃ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
4. ማመልከቻ ቅጽ/ፎርም በሁለት ኮፒ መሙላት/ማቅረብ (ማመልከቻ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
5. የአገልግሎት ክፍያ Euro 42.50
6. በፖስታ /Mail/ የሚልኩ ከሆነ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ ከነቴምብሩ አብሮ ይላኩ
አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት 4 ፎቶግራፍ (በከለር የተነሱት ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት፣ ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2. ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ
3. ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ገጽ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
4. በበኔሉክስ አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
» የመኖሪያ ፍቃድ ካርድ ወይም
» በሚኖሩበት አገር የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም የስራ ፈቃድ ማቅረብ
5. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (የአሻራ መውሰጃ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
6. ማመልከቻ ቅጽ/ፎርም በሁለት ኮፒ መሙላት/ማቅረብ (ማመልከቻ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
7. የአገልግሎት ክፍያ Euro 42.50
8. በፖስታ /Mail/ የሚልኩ ከሆነ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ ከነቴምብሩ አብሮ ይላኩ
በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት 4 ፎቶግራፍ (በከለር የተነሱት ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት፣ ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2. ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ
» የጠፋው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ገጽ ኮፒ ወይም የጠፋው ፓስፖርት ቁጥር
» በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ
» የፖሊስ ማስረጃ ፓስፖርቱ ስለመጥፋቱ
3. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (የአሻራ መውሰጃ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
4. ማመልከቻ ቅጽ/ፎርም በሁለት ኮፒ መሙላት/ማቅረብ (ማመልከቻ ቅጽ(ፎርም) ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ)
5. የአገልግሎት ክፍያ Euro 42.50
6. በፖስታ /Mail/ የሚልኩ ከሆነ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ ከነቴምብሩ አብሮ ይላኩ
ተጨማሪ ማብራሪያ
አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፣ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጣት አሻራ እንዴት ማቅረብ ይቻላል
በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው መላክ/መስጠት ይችላሉ፡፡
የጣት አሻራዎ ፓሊስ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች በሚሰጡበት የጣት አሻራ ማንሻ ወረቀት አስነስተው ቢያቀርቡ/ቢልኩ ይመረጣል፣ ካልሆነ የኤምባሲያችን የጣት አሻራ ፎርም ዳውንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ፡፡
የፓስፖርት አገልግሎቱ የሚፈጅበት ጊዜ
የሁሉም አይነት የፓስፖርት ማመልከቻ ከኤምባሲያችን ከደረሰ በኋላ ዋና መስራቤት(አዲስ አበባ) ተሰርቶ ለመምጣት በአማካይ ከ 6-8 ሳምንታት ይፈጃል:: እባክዎ ከጉዞ ቀን ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከቻዎ ያስገቡ!