Embassy of The FDRE to The Benelux & Permanent Mission to EU Institutions
Header

ኮንሱላር አገልግሎት(Amharic)

If you are not able to read this page, please download Ge’ez Font click here.

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡ በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ሲሰጥ የነበረው አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2010 ጀምሮ በኢምባሲያችን በኩል አገር ቤት ተልኮ መሰጠት ስለተጀመረ እባክዎ ከጉዞ ቀን ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ያቅርቡ/ይላኩ፡፡

አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡ እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ኢምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ግዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ግዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅበዎታል፡፡


የፓስፖርት አገልግሎት

የቪዛ አገልግሎት

የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት

የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት

የውክልና አገልግሎት

ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት